The Instant View Editor uses a three-column layout, so you really want to use it on a desktop screen that's wide enough. Sorry for the inconvenience.

Back to the main page »

Original

Preview

Link Preview

Issue #13

ከብሄራዊ ቴአትር እስከ ጣይቱ ባህል ማዕከል እና ኢሳት (ክፍል 2)
=================================
እሱ፣ በ1996 አካባቢ አንድ ሲዲ በይፋ በገበያ ላይ ባይውልም በየቦታው ግን ይሰራጭ ነበር፤ በመድረክ አመራሩ፣ በንግግሩ ፍጥነት፣ በአጫዋችነቱና በመድረክ ፈርጥነቱ በሰባዎቹ ድፍን ሀገር በፍቅር የወደቀለት የብሔራዊ ቴአትር መድረኮችን ሲያደምቅ የበዓላት የቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት ዝግጅቶችን በብዙ የድግግሞሽ ቀረጻና ከቀረጻ በኋላ በሚከወን በብዙ አርትኦት እንኳን በማይሳካ ብቃት ያሳምር የነበረ አንድ አርቲስት ታሪኩን እና ያሳልፋቸውን የሕይወት መሰናክሎች ከተወለደባት ከጎንደር ጀምሮ ከላይ ሳወራላት ግን ትንሹን ብቻ በቀነጨብቁላትላት በዓለምፀሐይ ወዳጆ መድረክ አጋፋሪነት በተካሄደ መድረክ ላይ በፊልም ፕሮጀክተር ታግዞ ዝናገር የተቀረጸ ቪዲዮ በሲዲው ላይ ነበር::
ታማኝ በየነ ይባላል:: በዓለም ዙሪያ ሀገራችንን ባህሏንና ኪነጥበቧን ለማስተዋወቅ ተዘጋጅቶ በነበረው የሕዝብ ለሕዝብ ኢትዮጵያ ኪነታዊ ጉዞ ላይ በጨፋሪነት እና በየሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደግሞ በኮሜዲ እንዲያዝናና
ከመታጨት ጀምሮ አንድ የድራም ተጫዋችን ለመተካት ወዲያውኑ ተለማምዶ መድረክ ላይ እስከመውጣት ድረሶ የሚያስደምም፤ እጅ እና እግሩን እስተባብሮ ድራሙን መጫወት ባለመቻሉም እግሮቹን ከፍቶ ሌላ ክራር ተጫዋች በእግሮቹ መካከል እግሩን አስገብቶ መድረክ ላይ ይረዳው እንደነበር ተናግሮም የመድረኩ ታዳሚዎች ሲያስቅ ተመልከተናል::
በእናት ሀገር ጥሪ ወጣቱ ሃገሩን ከጠላት እንዲጠብቅና እና እንዲዘምት በደርግ ዘመን በነበረ ቅስቀሳ ላይ ከሌሎች አርቲስቶች ጋር በመሆን ልብን በሚያሞቅ፣ ወኔን በሚቀሰቅስ የኪነት ስራ ከመሳተፉ በላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ከሰሜን እስከ ደቡብ ያሉ ሙዚቃዎችን እያዜመ በአዲስ አበባ ስቴዲየም እኛ አንድ ነን ሲል፣ ሰንደቅ አላማችንን ለብሶ በመድረኩ ላይ ሲጨፍር፣
"...ስሜ ለዋስትና የሚበቃ
ተግባሬም የመድረክ ጠበቃ..."
ብሎ ዝግጅቱን በፈጣን ንግግርና በግትም አዋዝቶ ሲመራ የሚፈጥረው ልዩ ስሜት
እንኳንን በግዜውና በቦታው ለነበሩት ቀርቶ ዘመናት አልፈው እንኳን ለሚያይ ሰው ዛሬም የማስደመም ኃይል አለው።
ታማኝ ከኢትዮጵያ ውጭም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስለሃገራችንን ታላቅነት በተከሸኑ ውብ ቃላትና በጥበብ በታሹ የመድረክ ዝግጅቶች ሲሰብክ በሚያወራው ሁሉ አለመስማማት ይከብዳል:: ለሀገሩ ካለው ልዩ ፍቅር በተጨማሪም ልዩ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰውን ትህትናውንና ሰው አክብሮቱን ስለሰራቸው ሥራዎች ምስጋና ለማቅረብ ወዳጆቹ ባዘጋጁትና በሚኖርበት በአሜሪካን ሀገር በተደረገ ግብዣ ላይ እንዲሁም በቅርቡ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ ጋር መድረክ ላይ በተገናኘ ወቅት በግንባሩ ወድቆ እስከመስገድ ድረስ ሲያሳይ ተመልክተናል::
ይኽንን ሁሉ ስብዕና ተላብሶ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) አስተዋጽኦ አበርካች እና ከፍተኛ የገንዘብ አሰባሳቢዎች መካከል አንዱ ከመሆኑ በተጨማሪ በዚሁ ጣቢያ ላይ ለተወሰነ ጊዜ "የታማኝ ሾው" አቅራቢ ሆኖ ቆይቷል:: እንዲያውም ከዚያ መርሐግብር ላይ ከቀረቡ ዝግጅቶች ውስጥ የተውውሰኑት የተቆራረጡ ቪዲዮዎች በማህበራዊ መገናኛ መካነ ድሮች ላይ ዛሬም ሲዘዋወሩ እና ሲጋሩ እናያቸዋለን::
ሁሉን ዘርዝረን ባንዘልቀውም እነዚህ ሁለት አርቲስቶች ኢትዮጵያን ሲናፍቋትና ኢትዮጵያም ስትናፍቃቸው ከርማ ወደሐገር ቤት የመግቢያቸው ቀን ተቆርጦ ነገ ማክሰኞ ነሐሴ 22 ዓለምፀሐይን ነሐሴ 26 ደግሞ ታማኝን ለመቀበል ኮሚቴዎች ተቋቋቁመው መሰናዶው ደምቋልና የዳሰሳ አዲስ ዝግጅት ክፍል አባላትም እነዚህን የኪነጥበብ አድባሮች የመምጣት ብስራት ለሁሉም አድናቂዎቻቸው እየተናገርን የምናገናቸውን መረጃዎች በተከታታይ ማድረሳችንን እንደምንቀጥል እንገልፃለን:: @AcessAddis
Declined by admin
Type of issue
Submitted via the Previews bot
Reported
Sep 7, 2018